አሜሪካ እና ስዊድን በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ 24 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ አሜሪካ ከ18 ሚሊየን ዶላር በላይ እና ስዊድን 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረጉ።
አሜሪካ ያደረገችው ድጋፍ በሱዳን ስደተኛ ጣቢያ ለሚገኙ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊ ነገሮችን ለማቅረብ እንደሚውል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።
ድጋፉ መጠለያ፣ ሀይል ሰጪ ምግብ፣ የጤና ክብካቤ፣ ለትምህርት፣ ለውሃ እና ንፅህና አገልግሎት እንደሚውል መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
በተመሳሳይ ስዊድን ያደረገችው ድጋፍ በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ፣ በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በኩል በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውል ተጠቁሟል።
በስዊድን መንግስት የተደረገው ድጋፍ ሀገሪቱ እስከአሁን ስታደርገው ከነበረው ድጋፍ ተጨማሪ መሆኑን በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!