የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢ ያላቸውን ልዩነት በውይይት ቢፈቱ ለቀጠናው መልካም መሆኑን ገለፀች፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያና ሱዳን ከሰሞኑ በስፋት እየተወራ ያለውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድና በንግግር እንደሚፈቱት እምነት እንዳላት ገልፃለች፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላትም አስታውቃለች፡፡
ስለሆነም ሁለቱ ሀገራት ለቀጣናዊ መረጋጋትና ብልጽግና ቁልፍ ሚና እንዳላቸው የጠቀሰው መግለጫው የተፈጠረውን ልዩነት በውይይት መፍታት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁሟል።
ለዚህም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ልዩነት ሊያባብስ ከሚችል ነገር በመቆጠብና በሰከነ መንገድ ማየት ያስፈልጋል ብላለች፡፡
ትብብር እና አጋርነትን በማስቀደም ሁለቱ ሀገራት ልዩነቶቻቸውን መፍታት አለባቸው ስትልም ሀገሪቷ በመግለጫዋ ጥሪ አቅርባለች።
ኢትዮጵያ በበኩሏ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ በማየት በውይይት እንዲፈታ ስትሰራ ቆይታለች፡፡
ሱዳንም በተመሳሳይ ወደ ጠረጴዛ ውይይት እንድትመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት በሰጡት መግለጫ ማሳሰባቸው አይዘነጋም፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!