የዚምባቡዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲቡሲሶ ሞዮ ህይወታቸው አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዚምባቡዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲቡሲሶ ሞዮ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ ዚምባቡዌ ታማኝ ህዝብ አገልጋዩዋን እና እውነተኛ ጀግናዋን አጥታለች ብለዋል።
ሲቡሲሶ ሞዮ ሙሉ የህይወት ዘመናቸውን ለዚምባቡዌ ነፃነት ሲታገሉ ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቱ ጓደኛየን አጥቻለሁ ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በምን ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ ይፋ ባያደርጉም አንድንድ መገናኛ ብዙሃን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ዘግበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የቀድሞው የዚምባቡዊ ፕሬዚዳንት ሮበር ሙጋቤ ከስልጣን እንዲነሱ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ነው ነውስ24 የዘገበው።
ሲቡሲሶ ሞዮ ሮበርት ሙጋቤ በፈረንጆቹ 2017 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!