Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ይርዳ የ2013 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በሀዲያ ዞን አስጀመሩ 

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2013  (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የ2013 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በሀዲያ ዞን አስጀመሩ፡፡

የተፋሰስ ልማት ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት  ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ÷ለጎርፍ እና ለመሬት መሸርሸር ተጋላጭ የሆነውን አካባቢ ተንከባክቦ ያቆየው የሀዲያ ህዝብ የአካባቢ ጥበቃ ጥቅምን በተግባር የሚያውቅ በመሆኑ ስለ አፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አይነገረውም  ብለዋል።

ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አመስግነዋል::

አያይዘውም ባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ተፋሰሶች ላይ በተገነቡ መስኖዎች አርሶ አደሩ ተጠቃሚ መሆኑንም ገልፀዋል::

በዛሬው እለት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች “የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን÷ በዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በክልሉ 357 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሥነ አካላዊ እና ሥነ ህይወታዊ ሥራ እንደሚከናወንም ገልጸዋል::

በተፋሰሶቹ ላይ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኝ በዘንድሮ አመት ብቻ ይተከላል ብለዋል::

የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ሥራ ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አርንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ለአንድ ወር በሚቆየው የተፈሰስ ልማት ዘመቻ ላይ በታታሪነት በንቃት እንዲሳተፉ አቶ እርስቱ ጥሪ አቅርበዋል::

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ሎምቢሶ  በበኩላቸው÷በሀዲያ ዞን በ2013 ዓ.ም 83 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በተፋሰስ እንደሚለማ  ተናግረዋል።

በክልሉ የ2013 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች  ፣ የደቡብ ብልፅግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ አቶ ሳኒ ረዲ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒትር ዲኤታ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.