Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት የተገነባው 12ኛውን ትምህርት ቤት በምዕራብ ጉጂ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ የተገናበው ኢፋ ሱሮ  ቡርጉዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የአሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ፣ አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ትምህርት ቤቱ 20 ሚሊየን በር ወጪ የተደረገበት ሲሆን የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካተዋል።

ፅህፈት ቤቱ በዛሬው ዕለት ያስመረቀው ኢፋ ሱሮ ቡርጉዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 12ኛው ነው።

በሁለት ፈረቃ 2 ሺህ 600 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በትምህርት ቤቱ አካባቢ እና አዋሳኝ ቀበሌዎች የሚገኙ ተማሪዎች እና ወላጆች ይህን እንድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.