ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ጥር 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑትን ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ።
በወቅቱም በኢትዮጵያ ለጃፓን ባለሃብቶች ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ትብብር ዕድሎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ከዚያም ባለፈ በውይይቱ ወቅት ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ÷ የኢትዮጵያን 10 ዓመት የልማት ዕቅድ ርዕይ፣ ዓላማዎች፣ ግቦች፣ ልዩ ባህርያት፣ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ የትኩረት መስኮች በዝርዝር አስረድተዋል።
አምባሳደሯም በበኩላቸው መንግስታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀው ÷በተለይም በመሰረተ ልማት ዘርፍ፣ በግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎች በጃፓን መንግስት የልማት ፖሊሲ ትኩረት የተሰጣቸው መስኮች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!