Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና በአየር ኃይል መካከል ያለው ትብብር በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ የተለያዩ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና በኢትዮጵያ አየር ኃይል መካከል ያለው ትብብር በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ የተለያዩ ዕድሎችን እንደሚፈጥርና እንዲሁም በዘርፉ ያለውን ደህንነት እንደሚያስጠብቅ ተገለጸ፡፡

ይህንን ያሉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ናቸው፡፡

ዋና አዛዡ ዩኒቨርስቲው የተቋሙን አቅም ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ተቋማቱ በጋራ መስራታቸው ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ለአየር ኃይሉ አስር የመማሪያ ሞጁሎችን አዘጋጅቶ ማስረከቡን አስታውቋል፡፡

የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሽፈራው ፈይሳ ዩኒቨርስቲው የተለያዩ ተቋማትና ብቃት ለማሻሻል የተጣለበትን ግዴታ እየተወጣ እንደሚገኝም በዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ በበኩላቸው ለተቋሙ አባላት ነጻ የትምህርት ዕድልና የረዥም እና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችንም እንደሚሰጥ አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም በስራው ለተሳተፉ የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች የዕውቅና ሰርተፊኬት መሰጠቱን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

 

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.