Fana: At a Speed of Life!

የ10 ዓመት የልማት እቅድ ኢትዮጵያን ከቀጠናው ሀገራት ጋር በልማት የሚያስተሳስር ነው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ዓመት የልማት እቅድ ኢትዮጵያን ከቀጠናው ሀገራት ጋር በልማት የሚያስተሳስር ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ የአስር አመቱ የልማት ዕቅድን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የልማት አጋሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር እያደረጉት ባለው ውይይት ላይ እንደተናገሩት፣ እቅዱ ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ጋር የተናበበ መሆኑ ቀጠናዊ ትስስርን ያጠናክራል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም የመንግስት እና የግል ተቋማት አብረው እንዲሰሩ በማስቻል መዋቅራዊ ለውጥን ለማምጣት ያስችላል ነው ያሉት።

ዕቅዱ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ ድህነትን በመቀነስ፣ የመዋቅር ለውጥ በማምጣት፣ የማይክሮ ኢኮኖሚ ክፍትን መሙላት ያስችላል ብለዋል።

በብስራት መለሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.