Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አስመልክቶ በቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 የሚካሄደውን ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ዞኖችን ህዝበ ውሳኔ አሰጣጥ አስመልክቶ በደቡብ ክልል አብይ የምርጫ ፀጥታ ኮሚቴ ክልላዊ እቅድ ላይ በሀዋሳ ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት በደቡብ ክልል 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና ፍትሀዊ እንዲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት ይሰራል፡፡
ምርጫው በህዝቡ ቀጥታ ተሳትፎ በአግባቡ ተካሂዶ የህዝብን ድምጽ ተከትሎ መንግሥት የሚመሰረትበት ነው ያሉት አቶ አለማየሁ ብቃት ያለው የጸጥታ አመራር በመስጠት የምርጫውን ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን መስራት ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል፡፡
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ያልፈታናቸው በመፍታት ሂደት ያሉና አሁንም ትኩረት ሰጥተን የምንሰራቸው ጉዳዮች አሉ ያሉት ሀላፊው በጅምር ላይ ያሉትን ጉዳዮች በፍጥነት በመፍታት መምራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምርጫን ተአማኒነትን የሚያሳጡ ከህጋዊና ህገ መንግስታዊ መርህ ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችንም በመከታተል ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ መምራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
አቶ አለማየሁ በደቡብ ምዕራብ አካባቢ ያለውን የህዝበ ውሳኔ ድምጽ የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.