Fana: At a Speed of Life!

በመስኖ ዘርፍ ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ፕሮግራም የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመስኖ ልማት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ጋር ለአምስት ዓመታት የሚቆይ በመስኖ ዘርፍ ተቋማዊ አቅም ግንባታ ስልጠና ፕሮግራም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የመስኖ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኢንጅነር ሳሙኤል ሁሴን እና የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ታምሩ ፍቃዱ ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ትኩረት የሚያደርገው በመስኖና ተያያዥ በሆኑ የአጫጭር የስልጠና ፕሮግራም ኮርሶች ላይ ነው ተብሏል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በመስኖ ዘርፍ የሚተገበረው የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ እቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናው የሚያተኩረው በፕሮጀክቶች ዕቅድ አወጣጥ ንድፍና ልማት፣ ፕሮጀክት አተገባበርና አመራር፣ የመስኖ ሲስተም ኦፕሬሽን፣ አስተዳደርና ጥገና፣ በሃይድሮሎጂና ውሃ ሃብት  እንዲሁም የመስኖ ልማት  በማህበራዊ- ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ላይ መሆኑ ነው የተጠቀሰው፡፡

በአምስት ዓመት ውስጥ በስልጠናው ከፌደራል እስከ ወረዳ የሚገኙ ከ34 ሺህ በላይ ባለሙያዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

በስልጠናውም በአምስት ዓመት ውስጥ ከ700 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግም ይገመታል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበትን ጉዳይ የመስኖ ልማት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በጋራ ያለውን ክፍተት እንደሚለዩ ነው የገለጹት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.