Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 950 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 950 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳታወቀው ክልሉ 950 ትራክተሮችን ለአርሶአደሩ ለማድረስ እየሰራ ይገኛል፡፡

የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራች እና የኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ የቦርድ አባላት በህንድ የጆን ዲር ኢንዲያ እና የፊልድ ኪንግ የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽን አምራች ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራው ይኸው ልዑክ ከኩባንያዎቹ ጋር መግባባት ላይ ደርሷል ብሏል ቢሮው፡፡

በዚሁ መሰረት ከጆን ዲር ኩባንያ ላይ በዚሁ አመት 950 ትራክተሮችን በመግዛት ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለአርሶ አደሮች ይሰራጫል ብሏል፡፡

ከትራክረሮቹ መሀከል 300 የሚሆኑት ባለ 75 ፈረስ ጉልበት ሲሆኑ ኩባንያው ሀደ ሀገር ቤት ማጓጓዝ ጀምሯል፡፡

በተጨማሪም ፊልድ ኪንግ ኩባንያ ከኬኛ ግብርና መሳሪያዎች ማረቻ ፋብሪካ ጋር በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ኩባንያው ለ950 ትራክተሮች መለዋወጫ ለማቅረብ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለቴክኒሺያኖች እና ለአርሶ አደሮች ለመስጠት፣  ከኬኛ ግብርና መሳሪያዎች ማረቻ ፋብሪካ ጋር በትብብር ለመስራት እና ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ ተቋም በሀገር ውስጥ ለማቋቋም ከስምምነት ደርሷል፡፡

ቢሮው እንዳስታወቀው ክልሉ የአርሶ አደሩን ህይወት ለመቀየር እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.