Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶች ለችግር ለተጋለጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በህገወጥ እና በኢ-ፍትሃዊ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶችን በማስለቀቅ ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እየተላለፉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ወራት ውስጥ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባካሄደው ሰፊ ጥናት በርካታ የቀበሌ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው በመገኘታቸው ለአቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሰጡ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አስታውሰዋል።
ይህን ተከትሎ ዛሬ በአራዳ ክፍለ ከተማ 139 በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶችን ግልፅ የሆነ መስፈርት በክፍለ ከተማው ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ማስረከብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ስራ ላስፈጸሙ የከተማ እና የአራዳ ክፍለከተማ አመራሮች እና ሰራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
እንዲሁም ምክትል ከንቲባዋ ዛሬ የቤት ባለቤት ለሆኑ ባለ ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን “የእናንተ ቤት የማግኘት መሠረት በህገወጥች ላይ በተደረገ ትግል የተገኘውን ድል በፍትሐዊነት ህዝብን ተጠቃሚ የማድረግ አቋማችን ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡
“በአሰራር ሥርዓት የታገዘ ፍትሐዊነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት ከተማችንን በአብሮነት ማበልፀግ እና ቃላችንን በተግባር የምናሳይበት እንደሆነ ላሳውቅ እወዳለሁ”ም ነው ያሉት፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.