Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ዋንጫ የሽኝት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ለተረኛው ክልል ለማስረከብ የሽኝት መርሐ ግብር ተካሄደ።

በመዲናዋ ቆይታው ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ገልጿል፡፡

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳስ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እና የፌዴራልና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ “ታላቁ ህዳሴን ለመገንባት ሳናጠና አልገባንም፤ ሳንጨርስ አናቆምም፤የብልጽግና ጉዟችን በህዳሴ ምእራፍ ውስጥ የሚደምቅ  የከተማችን ብሎም የሀገራችን ብርሃን ነው” ብለዋል፡፡

“ማደሪያ ላልነበረው ዓባይ ማደሪያውን ላበጃችሁ፤ ከታሪክ ተናጋሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት ላሸጋገራችሁን ፣ በዓለም አደባባይ ለአባይ ሞግታችሁ፣ የጉባ በረሃ ንዳድን ተቋቁማችሁ፣ በክብር ከዚህ መድረክ ላይ እንድንቆም ላበቃችሁን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ከልብ የሆነ ምስጋናን አቀርባለሁ”ም ነው ያሉት፡፡

ዓባይ ወንዝ ብቻ ሳይሆን ሃገር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ህዳሴ ግድብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መድመቂያ አርማና ኩራት ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

ዋንጫው በአዲስ አበባ ከተማ በቆየባቸው ወራትም በሁሉም ክፍለከተሞች ለግድቡ ግንባታ የሚሆን  ብር በቦንድ ግዢ እና ስጦታ እንዲሁም የህዝብ ተሳትፎ እና ንቅናቄ ስራ መሰራቱ ነው የተገለጸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.