በክልሎች መካከል ያለው የመሰረተ ልማት ስርጭት አለመመጣጠን እንዲስተካከል ባለድርሻዎች በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሎች መካከል ያለውን የመሰረተ ልማት ስርጭት አለመመጣጠን እና መጓደል ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠይቋል።
በፌዴራል የመሰረተ ልማት ተቋማት የስርጭት መስፈርት ዝግጅት እና በጋራ ገቢዎች አስተዳደርና ማከፋፋያ ቀመር አፈፃፀም ላይ ለፌዴራልና ለክልል ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በመክፈቻ ንግግራቸው ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 62(4) የተሰጡትን ስልጣን እና ተግባር በመፈፀም ፍትሃዊነት ማረጋገጥ፣ የህዝብን እኩልነት እንዲኖር መስራት እንዲሁም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።
የህገ መንግስቱን ዋነኛ አላማ ዜጎች በእኩልነት መልማት እንዳለባቸው ያመለክታል ያሉት አፈጉባኤው ሁሉም እኩል የመልማት ከልማቱም የመጠቀም መብትን ባረጋገጠ መልኩ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የመሰረተ ልማት ስርጭት ጉድለትን መፍትሄ ለመስጠትም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እና የስርጭት ቀመር አፈጻፀምን በሚገባ መገምገም እንደሚገባ ተመልክቷል።
አቶ አደም እንዳሉት የስርጭት ሲባል ሁሉንም ማዳረስ ሳይሆን በየአካባቢው ያሉ እምቅ ፀጋዎች መጠቀም ማለት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ህግ አውጭው እና ህግ አስፈፃሚው በጥምረት ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።
በወይይቱ ኢትዮ- ቴሌኮም፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እንዲሁም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች፣ የፌዴራል መንገዶች ባለስልጣን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ክልላዊ የመሰረተ ልማት ስርጭትን በተመለከተ ውይይት እና ግምገማ ይካሄዳል።
በዚህ መድረክ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እና የዘርፍ ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!