የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታዋ ከሴንት ፒተርስበርግ የኢንቨስትመንት ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ዲፕሎማሲና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ ከሩሲያ ሴንትፒተርስበርግ ከተማ የኢንቨስትመንት ልዑካን ጋር ተወያዩ፡፡
ሚኒስትር ዲኤታዋ ባለሀብቶቹ ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ በማድረጋቸው አመስግነው፥ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታ በማብራራት መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ወደ ተግባር እንዲገቡ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል፡፡
የልዑኩ መሪ ማርክ ሩስላን በበኩላቸው በነበራቸው የስራ ጉብኝት ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተደረገላቸው አቀባበበልና ውይይት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ልዑኩ በሶስት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለመሰማራትና በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አብራርተዋል፡፡
ቡድኑ በተለያዩ ሃገራት በተግባር የተደገፈ እንቅስቃሴ እንዳለውና በጅቡቲ በቱሪዝም ዘርፍ ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን በመግለጽ፣ በኢትዮጵያም በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንቅስቃሴ እንደሚገባ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				