Fana: At a Speed of Life!

የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመፍታት ጠንካራ የማስፈጸም አቅምን መገንባት ላይ በትኩረት ይሰራል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ተቋማት የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመፍታት ጠንካራ የማስፈጸም አቅምን መገንባት ላይ በትኩረት ይሰራል ተባለ ።.

የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የማስፈጸም አቅም ግንባታ ማሻሻያ ጥናት ዙሪያ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደበት ነው።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሀይሉ ሉሌ ጥናቱ ውጤታማ የህዝብ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ የተቋማት አሰራርና አደረጃጀት ፣የሰው ሃብት ብቃት ማጎልበት በዝርዝር በመዳሰስ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ገልጸዋል ።

በዋነኛነት የህብረተሰቡን የአገልግሎት ፍላጎት እና እርካታን ለማሳደግ የታዩ ለውጦችን በይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል ።

በአብዛኛው ተቋማት በአመራር በኩል የአገልጋይነት መንፈስን ለማጽረስ እና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት አበረታች ቢሆንም በተወሰኑ ተቋማት እና ወረዳዎች የተነሳሽነት ችግሮች መኖሩን አንስተዋል ።

በውይይቱ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ሌሎችም የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በሴክተር መስሪያቤቶች፣ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የአገልግሎት አሰጣጥ የሱፐርቪዥን ግኝት ቀርቧል።

በተጨማሪም የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የ10 አመት ፍኖተ ካርታ እና ውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ማሻሻያ ላይ ውይይት መደረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.