Fana: At a Speed of Life!

የፊንላንድ መንግሥት በአማራ ክልል የሚያደርገውን የፕሮጀክቶች ትግበራና ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፊንላንድ ኤምባሲ የልማት ትብብር ጉዳዮች ኃላፊ አርቶ ቫልጃስ ከአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋር ትብብራቸውን በሚያጠናክሩበት ጉዳይ ላይ ተወያዩ።

የፊንላንድ መንግሥት በአማራ ክልል በግብርና፣ በገጠር የንጹህ መጠጥ ውኃና በጤና አጠባበቅ፣ በመሬት አስተዳደርና በትምህርት ዘርፍ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ያደርጋል።

አርቶ ቫልጃስ እንዳሉት በአማራ ክልል ተግባራዊ እያደረጓቸው ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን ኑሮ የሚያሻሽሉና ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ናቸው።

በቀጣይም ከክልሉ የ10 ዓመታት ስትራቴጅክ እቅድ ጋር የሚጣጣሙ ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው የፊንላንድ መንግሥት በአማራ ክልል ተግባራዊ እያደረጋቸው ያሉ ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የፊንላንድ መንግሥት በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በትብብር እንደሚሠራ መግለጻቸውንም አብመድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.