Fana: At a Speed of Life!

25 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ሃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ሃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

በስምምነት መድረኩ ላይ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሃገሪቱ ስምንት ክልሎች የተመረጡ የገጠር ከተሞች ላይ ግንባታው የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት ከ145 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ግንባታው ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 20 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እና በኢትዮጵያ መንግስት በሚሸፈን 161 ሚሊየን ብር ይከናወናል ነው የተባለው፡፡

ግንባታው በስድስት ወራት ይጠናቀቃል የተባ ሲሆን፥ በሶስት የቻይና እና በአንድ የኮሪያ ኩባንያዎች እንደሚከናወንም ተገልጿል፡፡

ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ስምንት ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን 68 ነጥብ 7 መካከለኛ እና 233 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ የመስመር ዝርጋታንም ይሸፍናል ተብሏል።

በ2012 የተጀመሩ 12 የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ አሁን ላይ ስምንቱ ተጠናቀው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ ቀሪ አራቶቹም በቅርብ እንደሚጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ 125 አዳዲስ የገጠር መንደሮችን የሃይል ጠቃሚ ማድረግ ስለመቻሉም በስምምነቱ ወቅት ተነስቷል።

በይስማው አደራው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.