የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች በቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በድሬዳዋ እየተወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች በቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በድሬድዋ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የአፋር፣ የሶማሌ፣ የኦሮሚያ፣ የሃረሪ ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃይሎች በአሁናዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ነው በድሬድዋ ከተማ እየመከሩ ነው የሚገኙት።
የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ በቀጣናው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን፣ አልሸባብንና ሌሎች ፀረ ሰላም ሃይሎችን ከመቆጣጠር አንፃር ህገ ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሃይሉ ያለውን ዝግጁነት ይዳሰሳል ብለዋል፡፡
እንዲሁም አጠቃላይ ከአዳማ እስከ ጅግጅጋ – ጅቡቲ ያለውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ ያሉ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው፡፡
በውይይቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያና የክልሎች ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣናት መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!