ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳና አካባቢዋ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳና አካባቢዋ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አደረጉ፡፡
የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት በሀገሪቱ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ ወገኖች እንክብካቤ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች የዊልቸር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ቀዳማዊ እመቤቷ ዛሬም በደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች ተገኝተው ለ28 አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉ የተገኘው ሞቢሊቲ ወርልድ ከተባለ ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባው የአብ ሜዲካል ሴንተር ከተባለ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ተብሏል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!