ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ልማት ፈንድ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ልማት ፈንድ ተወካይ ወይዘሮ ዴኒያ ጌይል ጋር ተወያይተዋል፡፡
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ፈንድ ተወካይ ወይዘሮ ዴኒያ ጌይል ጋር በተለያዩ ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በጋራና በትብብር ሊከወኑ ስለሚችሉ ሥራዎች ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ በፕላንና ልማት ኮሚሽን ሥነ ሕዝብ ልማት ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ወይዘሮ ዴኒያ ጌይል በፕላንና ልማት ኮሚሽን ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
ሁለቱም ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ ሕዝቡ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ልማት ውስጥ የሚጫወተውን ጉልህ ሚና ከግምት በማስገባት አጋርነታቸውን ማጠናከሩ አስፈላጊ እንደሆነ አስምረውበታል፡፡
በተጨማሪም ከቀደሙት የአተገባበር ክንውኖች ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጉዳዮችም የውይይቱ ትኩረት እንደነበሩ ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!