የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመኖሪያ ቤቶችን ሊያስገነባ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንደስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡
የከተማውን የቤት አቅርቦት ችግር ይቀርፋል የተባለው ይህ ፕሮጀክት በአራት ዙር ግንባታ የፓርኩን ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በከተማው ውስጥ ያሉ ነዋሪዎችንም ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመቀናጀት ፓርኩ ካለበት ቦታ ጀምሮ ከ3 እስከ 5 ኪሎ ሜትር ውስጥ ያሉ ህጋዊ ይዞታ ያላቸው ግለሰቦችም እስከ 350 ሺህ ብር ብድር እንዲያገኙ በማመቻቸት ቤቶችን ገንብተው ለተከራዮች እንዲያቀርቡ የሚያስችል አሰራርም የዕቅዱ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ከከተማው ማዘጋጃ ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ጋር በመተባበር ዕውን የሚሆነው የቤቶቹ ግንባታ ከከተማዋ የዕለት ተዕለት ዕድገትና ለመኖሪያነት ምቹ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የሚጨምረውን የነዋሪዎች ቁጥር ለማስተናገድ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል መባሉን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!