የሲዳማ ክልል የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ልዩ የስፖርት እንቅስቃሴና ውድድር በሐዋሳ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልል የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ልዩ የስፖርት እንቅስቃሴና ውድድር በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ።
በነገው ዕለት የካቲት 15/2013 ዓም የሚከበረውን የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል በሐዋሳ ከተማ ልዩ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴና ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሂዷል።
የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከለሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ከተከናወኑ ውድድሮች መካከል በሐዋሳ ከተማና በሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች መካከል የተካሄደ የእግር ኳስ ውድድር አንዱ ሲሆን የብስክሌት ውድድር፣ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ፣ የቴኳንዶ ስፖርት፣ ስኬት ቦርዲንግና ሌሎች አዝናኝ ውድድሮችና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የፕሮግራሙ ድምቀት ነበሩ።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬ በአካል ብቃት እንቅስቃሴና ስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ዜጋ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጣ፣ ለሀገራችን ብልፅግናና ለተሻለ ነገ ድርሻው የጎላ ያለው መሆኑን ገልፀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!