Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ2013 የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ዘላለም መንግስቴ “ግምገማው የቢሮውን የ6 ወራት አፈፃፀም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በአግባቡ በመፈተሽ ለቀጣይ ስራ ላይ አቅም ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው” ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ፣ የፎረንሲክ ምርመራ ምክትል ዘርፍ እና የድጋፍ ሰጪ ዘርፍ የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚካሄድ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.