በሲዳማ ክልል 125ኛው የአድዋ ድል በአል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ደረጃ 125ኛው የአድዋ ድል በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
በዓሉ ከሲዳማ ባህል ፌስቲቫል ጋር በጥምረት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን፤ በዓሉን አስመልክቶ የሲዳማን ባህል የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ቁሳቁሶችና አልባሳት እንዲሁም የሲዳማ ባህላዊ ምግብ አውደ ርዕይ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል።
በአሉን በማስመልከት በአድዋ ድል ዙሪያ የሚያጠነጥን ሰነድ በታሪክ ምሁራን ቀርቦ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል።
በበዓል ስነ-ስርአቱ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ከክልሉ ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የተውጣጡ የመስተዳድር አካላትና የህዝብ ተወካዮች፣ የጥንት አርበኞች እንዲሁም የኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች ተወካዮች፣ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጅቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ በዓሉን በማስመልከት የተለያያዩ ትእይንቶች እያቀረበ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!