Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር   ለሲዳማ ክልል ማቋቋሚያ የሚሆን የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤ.ቢ.ሲ)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሲዳማ ክልል ማቋቋሚያ የሚሆን የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ምክትል ከንቲባ  ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የሲዳማ ክልል የምስረታ ክብረ  ዓል ላይ በመገኘት የሲዳማ ክልል ሆኖ በመመሰረቱ  የእንኳን ደስ አላችሁ  በማለት  የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ህዝቦች ነጻነታቸው ሲረጋገጥ፣ጥያቄያቸው ሲመለስ ፤እራሳቸውን በራሳቸው ሲያስተዳድሩ ኢትዮጵያ የምትፈርስ የሚመስላቸው አካላት የሲዳማ ክልል ሆና  ስትመሰረት መላው  ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ሰብስባ የኢትዮጵያዊነት ድምቀት ፣ዉበት በአንድ ላይ የደስታው ተካፋይ በማድረግ ኢትዮጵያ አንድ መሆኗን በተግባር አሳይቶናል ብለዋል ።

አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን ከተማ ናት ያሉት ወይዘሮ አዳነች የሲዳማ ህዝቦች ትውፊታዊ ባህልን በከተማዋ የባህል ማዕከል እንደሚካተት ተናግረዋል።

በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ከሲዳማ ክልል ጋር ያለውን ግንኙነት በይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና የሀዋሳ ከተማ የአዲስ አበባ እህት ከተማ በመሆን አብረን እንበለጽጋለን በማለት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መግለጣቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.