Fana: At a Speed of Life!

125 የአድዋ ድል በዓል በባህርዳር ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ125ኛው የአድዋ ድል በባህርዳር ከተማ በሙላለም የባህል ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡

በበዓሉ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብርሀም አለኸኝን  ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ  አመራሮች የተገኙ ሲሆን፤ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ አባት አርበኞችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ  የህብረተሰብ  ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ብዙነሽ መሰረት እንደተናገሩት፤ የአድዋ ድል ነጮች በጥቁር ህዝቦች ላይ ያደርሱት የነበረውን ወደር የለሽ ጭቆና፣ ብዝበዛ እንዲሁም በደል ያስቆመ ነው፡፡

የአድዋ ድል በዓል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው በነበራቸው ህብረብሔራዊ ፍቅር ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተሰባስበው በመዝመት  ያስገኙት ድል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አድዋ ለአሁኑ ትውልድ የሀገር አንድነት ግንባታ ስርዓት ትልቅ ትምህርት እንደሆነም ነው የገለፁት፡፡

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤትና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ አቶ አብረሃም አለኸኝ በበኩላቸው የአድዋ ድል ለኢትዮጵያም ሆነ ለመላው አፍሪካዊ እና ለጭቁን ህዝቦች  ድል ነው ብለዋል፡፡

አድዋ የአፍሪካውያን  የድል ጮራ በመሆኑ አፍሪካውያን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በሰንደቃቸው እንደሚጠቀሙበትም ነው የገለጹት፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.