Fana: At a Speed of Life!

ሦስት ክልሎች ለትግራይ ክልል የለገሱትን 282 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ ክልሎች ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋሚያ የለገሱትን 282 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረከቡ።
ድጋፉን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰንና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስረክበዋል።
የኦሮሚያ ክልል 257 ሚሊየን ብር፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ 15 ሚሊየን ብር እና የጋምቤላ ክልል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ነው የደገፉት።
በተጨማሪም የጋምቤላ ክልል ሁለት፣ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ደግሞ አንድ አምቡላንስ ለግሰዋል።
ርዕሰ መስተዳድሮቹ ድጋፉን በመቀሌ ከተማ በመገኘት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ አስረክበዋል።
ዶክተር ሙሉ በዚሁ ወቅት ክልሎቹ ላደረጉት ድጋፍ በክልሉ ሕዝብ ስም አመስግነዋል።
በርክክቡ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የትግራይ ክልል ኮማንድ ፖስት ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ተገኝተዋል።
የትግራይ ክልል የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎችም ለርዕሰ መስተዳድሮቹ ስጦታ ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.