Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የይርጋአለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስመርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከፌዴራልና ከክልል አመራሮች ጋር በመሆን የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀዋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየተገነባ ያለው የፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በከፊል ምርት ጀምሯል፡፡

እስካሁን ከተገነቡት 11 የምርት ቦታዎች ውስጥ 4 ቱ በማምረት ላይ ናቸው፡፡

8 ተጨማሪ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የገበያ ትስስር እና ሌሎች ፍላጎቶችን በመፍጠር የማሽን ተከላ ከተጠናቀቀ በኋላም ምርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት በአቮካዶ ዘይት ፣በማር እና በቡና ኪኒን ማቀነባበር ላይ መሰማራታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.