የአሶሳ ነዋሪዎች የውጭ ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የውጭ አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።
ሰላማዊ ሰልፉ የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከዳር ለማድረስ ያላቸውን ዝግጁነትና ቁርጠኝነት የሚገልጹ መፈክሮችን ይዘው በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።
“አሜሪካና ምዕራባዊያን በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ተፈጻሚ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ነጻ ነበርን፤ ነጻነታችንን እናስቀጥላለን፣ አባይን ከመገደብ ማንኛውም ሃይል አይመክተንም” የሚሉ ይገኙበታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!