Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)6ኛው ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች ሰዓታት ብቻ የቀረውን ምርጫ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ሁሌም የሚታወስና ተዓማኒነቱም የተረጋገጠ ሆኖ እንዲያልፍ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ነው የገለፁት።

መራጩ ማህበረሰብ የምርጫ ካርድ መውሰድ የዴሞክራሲ መንገድ ጅማሮ እንጂ ግብ አለመሆኑን በመገንዘብ በምርጫው ቀን ድምፅ ለመስጠት እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርበዋል።

ነዋሪዎቹ የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን ውጤቱን በፀጋ ተቀብለው ለሀገር እና ዜጎች ሰላም ዘብ ለመቆም ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል።

በከተማዋ 89 ምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፥ ከ113ሺሀ በላይ መራጮች ካርዳቸውን በእጃቸው አስገብተዋል።

ከነዚህም ውስጥ ከ54ሺህ በላይ ሴቶች መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የግል ተወዳዳሪም እጩዎቻቸውን በማቅረብ ይወዳደራሉ።

በአፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.