Fana: At a Speed of Life!

“ነገ ማልደን እንመርጣለን ” – የደብረ ማርቆስ ከተማ  ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)”ነገ ማልደን እንመርጣለን ”  ሲሉ የደብረ ማርቆስ ከተማ  ነዋሪዎች ገለጹ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የከተማዋ ኗሪዎች÷የምርጫ ካርዳቸውን ተጠቅመው ይበጀኛል የሚሉትን የፓለቲካ ፓርቲ እንደሚመርጡ ተናግረዋል ።

ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የሚጠበቅብንን ሃገራዊ ሃላፊነት እንወጣለን ብለዋል ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ምርጫ ምክትል አስተባባሪ አቶ ብርቁ ሁነኝ ÷ምርጫውን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ለሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ደርሰዋል ነው ያሉት።

ቀደም ብሎ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ሰነድ ተዘጋጅቶ የጋራ ስራዎች ሲከናወኑ እንደቆየ ያነሱት አቶ ብርቁ÷  የጎላ እንከን አላጋጠመንም ብለዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን 1ሺህ 451የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን ÷18 ያህል የምርጫ ክልልሎች ይገኛሉ።

ነገ ሰኔ 14 ከማለዳ ጀምሮ ዜጎች ድምጽ ይሰጣሉ ።

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.