Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በ13 ዘርፎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪን በድሪ የክረምት የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎትን በይፋ አስጀመሩ።

የአረጋውያን የቤት እድሳትን በጂኔላ ወረዳ በመገኘት ያስጀመሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በንጉስ ሺራ ትምህርት ቤት በመገኘትም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ መሠማራታቸው ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባለፈ የአዕምሮ እረፍት በመስጠቱ ረገድ ያለው ድርሻ የጎላ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

በክልሉ በ2012 ዓ.ም የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ አስተዋፅኦ መደረጉን የገለፁት ደግሞ የክልሉ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ናቸው።

በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኢትዮጵያን እናልብሳት በሚል መርህ ቃል እስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም በሚዘልቀው የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ወጣቶቹ በ13 ዘርፎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.