Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል   የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ የካንትሪ ፕሮግራም ዳይሬክተርና የምስራቅ አፍሪካ ማዕከል ኃላፊ ከሆኑት ከዶክተር አብዱል ካማራን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም እየተገነቡ ባሉት የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ወደፊት በአማራ፣ ደቡብ ክልልና ምስራቅ ኦሮምያ በሚገነቡት 3 ፓርኮች ስለሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል።

በውይይታቸውም የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፓርኮቹ ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ ዶክተር አብዱል ካማራ ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.