Fana: At a Speed of Life!

የህውሃት የሽብር ቡድን በትግራይ ከተሞች ነዋሪዎች ላይ ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛል- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህውሃት የሽብር ቡድን የመከላከያን የተናጠል ተኩስ አቁም እና ከቐለ መውጣት ተከትሎ መቐለ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በመግባት በክልሉ ነዋሪ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
በመቐለ እና በሌሎች ከተሞት ከጊዚያዊ አስተዳሩ እና መከላከያን ተባራችኋል ያላቸውን ንጹሃን ላይ ግድያ እየፈጸመ ሲሆን ይህንም ተግባሩ የትግራይ ያለውን የሰብዓዊ አቅርቦቶች እጥረት አባብሶ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡
በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ መንግስት ያደረገውን አይነት የተኩስ አቁም ከማድረግ ይልቅ የኢትዬጵያን እና የአለማቀፉን ማህበረሰብ በሃሰተኛ የድል ፕሮፓጋንዳዎቹ ለማታለል እና ትኩረት ለማግኘት በሚያደርገው መፍጨርጨር የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪዎችንና የዜጎች ደህንነት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እያስገባ እንደሆነ ኢትዬጵያዊያን እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ሊረዳ ይገባል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.