በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እያከናወኑ ነው- ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ሳያቋርጡ እያከናወኑ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ይህንንም ሚኒስቴሩ ትግራይ ከሚገኙ ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር ባደረገው ክትትል ማረጋገጡን ነው የገለፀው፡፡
የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችም ቦታው ድረስ በመገኘት የተማሪዎችን ድምጽ በመቅረጽ ለተማሪ ቤተሰብና ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ በማሰማታችሁና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰጠ ያለውን መረጃ በተጨባጭ ማስረጃ ስላረጋገጡ ሚኒስቴሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!