Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለፃ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ገለፃው የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ስርጭትን ጨምሮ ሰብዐዊ እንቅስቃሴዎችን ለመፍታት ያለመ ሲሆን÷ በትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ተወካዮች እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መገኘታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.