Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛ ዙር 6ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ረቂቅ አዋጆችን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በ2ኛ ቀን ውሎው በቀረቡለት የጌዴኦ ባህላዊ መልክኣ ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ የወጣ ረቂቅ አዋጅ ፣የክልሉ ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅና ደንብ ላይ ከተወያየና ማዳበሪያ ሀሳቦችንና አስተያየት ከሰጠ በኋላ አጽድቋል።
በተለይ በቅርስ ጥበቃ ረገድ በክልሉ በርካታ የህዝብ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች በመኖራቸው ለሌሎችም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አባላቱ አሳስበዋል።
ረቂቅ አዋጆች በሙሉ ድምጽ ሲጸድቁ አንዱ የዋና ኦዲተር ማሻሻያ ደንብ ደግሞ በሁለት ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.