Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 3ኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
 
ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ÷ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
 
በአንድ ቀን ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።
 
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመርም ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያመላክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡
 
በቅድስት ተስፋዬ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.