Fana: At a Speed of Life!

በውጊያ ስንጠቃ የጁንታው አመራር አባላት ጥለውን ሸሹ – ምርኮኛ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ውጊያው እየበረታ ሲመጣ የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች ጥለውን ይሸሹ ነበር ሲል ምርኮኛው በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ይገልጻል፡፡

ወጣት ካዕላይ መንበር ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል ሀገረ ሰላም ወረዳ ደዋ ተንቤን በሚባል አካባቢ ነው።

አቅመ ደካማ ወላጆቹን ለመርዳትና የራሱንም ህይወት ለመለወጥ ሲል ከደዋ ተንቤን ወደ መቀሌ በመሄድ የግል ስራ ጀመረ።

ወጣት ካዕላይ መቀሌ በተከራያት አነስተኛ ቤት የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ በመጀመር ራሱንና አቅመ ደካማ ወላጆቹን እየረዳ ህይወቱን መምራቱን ቀጠለ።

የኋላ ኋላ ግን “ለፍቶ አዳሪው” ካዕላይ በክፉ ተመልካቾች ዓይን ወስጥ ገባና “ለሌላ ስራ ፈልገንሃል” በሚል ተመለመለ።

የአገር መከላከያ ሰራዊት የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ተከትሎ አሸባሪው ህወሃት ከየበረሃው ተሰባስቦ የጥፋት ዘመቻው አካል ለማድረግ ነበር ወጣት ካዕላይን የመለመለው።

ከሌሎች ህፃናትና ወጣቶች ጋር ኩይሃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሄድ የሶስት ቀን ወታደራዊ ስልጠና እንደወሰደም ወጣቱ ይናገራል።

ከስልጠናው በኋላ ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም ወዴት እንደሆነ እንኳን ሳይነገራቸው ከሌሎች ወጣቶች ጋር በሌሊት ጉዞ በማድረግ
በውጊያው ወቅት እርሱ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ሳይኖረው ለውጊያ እንዲሰለፍ መደረጉንም ገልጿል።

በእለቱ ውጊያው እየበረታ ሲመጣ ለመሸሽ ቢሞክርም እንደማይቻልና “ከሞተ ወይም ከቆሰለ ጓደኛው” መሳሪያ በመውሰድ እንዲዋጋ የቅርብ አዛዦቹ እንዳስገደዱትም ነው የተናገረው።

በዚህ ወቅት በውጊያው እየተጠቁ ሲመጡ አመራር አባላቱ ሲሸሹ ካዕላይም በሚያመልጥበት ወቅት እግሩ ላይ ተመትቶ እንደወደቀ አጋጣሚውን በሃዘን ያስታውሰዋል።

በቅፅበት የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እያጠቃ አጠገቡ በመድረሱ እጁን በመስጠት፤ ልዩ ሃይሎቹ ወዲያው የሚደማውን እግሩን አስረው ወደ ህክምና እንዳደረሱትም ገልጿል።

“የትግራይ ወጣት ባረጁ ፖለቲከኞች መታለል የለባቸውም” የሚለው ካዕላይ÷ ከእርሱ ህይወት ትምህርት መውሰድ “እኔ ከሞትኩ…” በሚል አስተሳሰብ ትውልድ ለማስጨረስ ቆርጦ የተነሳውን አሸባሪ ሃይል መዋጋት እንዳለባቸው መልዕክት ያስተላልፋል።

በአፋር ዱበቲ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኘው ካዕላይ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።

አሸባሪው ህወሓት ታዳጊ ህጻናትን ጭምር ለጦርነት በመመልመል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.