Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው ህወሓት ሲጠፋ ነው-ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲጠፋ መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡
የብልጽግና፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ፓርቲ አመራሮች በጋይንት ግንባር ጨጨሆ ተገኝተው የመከላከያ ሰራዊቱን ተጋድሎ ተመልክተዋል።
አሸባሪው ቡድን በከተሞች ላይ ከፍተኛ በቀል እና እና ውድመት መፈጸሙን የተናገሩት አመራሮቹ÷የቡድኑ አላማም መግደል፣ ማፈናቀል፣ ንብረት መዝረፍ እና ማውደም መሆኑን አንስተዋል፡፡
አመራሮቹ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በአጭር ጊዜ ተባብረን ሙሉ በሙሉ እንደመስሰዋለን ብለዋል።
በቡድኑ የወደሙ የግለሰብ እና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ በቅንጅት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡
ዛሬ ጨጨሆ የተገኙት የተፎካካሪፓርቲ አመራሮች ከብልጽግና አቶ ዮሀንስ ቧያለው እና አቶ ፈንታ ደጀን፣ ከኢዜማ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ከአብን አቶ ጣሂር ሙሀመድ እንዲሁም ከአዴሃን አቶ ተስፋሁን አለምነህ ናቸው።
በዙፋን ካሳሁን እና ምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.