Fana: At a Speed of Life!

የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአቶ ደረጀ ሀብተወልድ አስተባባሪነት የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ከ1 ነጠብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ለመከላከያ የሠራዊት አባላት የሚዉል ነዉ፡፡

ድጋፉ በሀገር ዉስጥ እና በባሕር ማዶ የሚገኙ የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ያደረጉት መሆኑን የገለጹት አቶ ደረጀ ሀብተወልድ÷ በተለይ በዚህ ወቅት መረዳዳት እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

አቶ ደረጀ የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለተፈናቃይ ወገኖች አለናችሁ ያሉ ሲሆን÷ ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ኢንጅነር ከማል ሙሀመድ አቶ ደረጀ ሀብተወልድ እና የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ሌሎች ወገኖችም ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ከንቲባዉ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.