Fana: At a Speed of Life!

በሃዋሳ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ በተደረገ ቁጥጥርና ድንገተኛ ፍተሻ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 48 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የንግድ ተቋማቱ ባለቤቶችም በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉንም ቢሮው አስታውቋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ፍቃዱ ጳውሎስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት÷ ህገወጥ ነጋዴዎች በተለይም በምግብ ነክና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ አላስፈላጊ ዋጋ በመጨመር የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ችግሩን ለመፍታትም የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ክልሉ ከሚያስገቡ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ይህን ተከትሎም በክልሉ በተለይም በሐዋሳ ከተማ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ የንግድ ተቋማት ተለይተው እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የምርት እጥረት ባለበት መንግስት ድጎማ የሚያደርግባቸው ስኳርና ዘይት የመሳሰሉ ምርቶች በበቂ መጠን ለህብረተሰቡ ተደራሽ አለመደረጉን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ከፊቤላ የዘይት ኢንዱስትሪ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት በዚህ ሳምንት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በሁለት የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች በኩል የምግብ ዘይት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው ያሉት የቢሮው ኃላፊ÷ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሊትር ዘይት ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓትና ልማት ድርጅት በኩል 550 ሺህ ሊትር ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች በኩል ወደ ክልሉ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.