በኮሎራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ኮሎራዶ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 100 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ገንዘቡን ካዘጋጇቸው ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
ገንዘቡንም ለዚሁ አላማ እንዲውል በተከፈተው የባንክ አካውንት ገቢ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ግድቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ እስኪገባ ድረስም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!