Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዓመት ካጋጠሙን ፈተናዎች ወጥተን ስኬት ለማስመዝገብ በትኩረት የምንሠራበት ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አዲሱ ዓመት ከዚህ ቀደም ካጋጠሙን ፈተናዎች ወጥተን ስኬት ለማስመዝገብ በተለየ ትኩረት የምንሠራበት ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልለ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የ2014 ዓ.ም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው የተጠናቀወቀው 2013 ዓ.ም እንደሃገርም ሆነ እንደክልል በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ለሃገራቸው ህልውና አንድነታቸውን ለዓለም ያሳዩበት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በርካታ የውጭና የውስጥ የጥፋት ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም በኢትዮጵያዊያን አንድነት ጥረታቸው የከሸፈበት ዓመት ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በመነሳቱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተላላኪዎቹን አሠማርቶ ጉዳት አድርሷል ያሉት አቶ አሻድሊ ይህንን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ተነስተዋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ዓመቱ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አንድነታችን የበለጠ ተጠናክሮ የታየበት እና ኢትዮጵያዊያን በችግር ወቅት በጋራ እንደሚቆሙ ለዓለም ያሳዩበት እንደሆንም ተናግረዋል፡፡

ከተጠናቀቀው 2013 ዓ.ም ትልቅ ትምህርት በመውሰድ በ2014 አዲሱ ዓመት ሠፊ ሥራ የሚሠራበት እና የጎደሉትን በመሙላት ስኬት የሚመዘገብበት ሥራ ከሁሉም እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል፡፡

ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ ካጋጠሙን ችግሮች ወጥተን ስኬት የምናስመዘግብበት ዓመት እንዲሆንም መመኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.