Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት የሽብር ቡድን በግፍ ለተረሸኑ መታሰቢያ እና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በጋይንት እና አካባቢው የህውሓት የሽብር ቡድን በግፍ ለተረሸኑ እና ሀገራችን አናስደፍርም ብለው አንገት ለአንገት ተናንቀው ህይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ተደርጓል።
ድጋፉ ለተሰው፣ ለቆሰሉ እና ለተደፈሩ ሴት እህቶች እና እናቶቻችን ”መከታ ለወገን” ከተሰኝ በውጭ ሃገር እና በሃገር ውስጥ ከሚገኙ ወገኖች የተሰበሰበ ገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ፥ የተሰው ወገኖች ለሃገር ክብር ሲሉ በመዋደቃቸው ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ እኛም ከተጎዱ ወገኖች ጎን ነን ብለዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፖርቲ ሀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፥ ትግሉ አለበቃም አሁንም ከህዝቡ ጋር በመሆን ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የ34ኛ ክፋለጦር አመራር ኮሎኔል ሽጉጤ አቡሃይ ፥የህውሓት የሽብር ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች በርካታ ጥፍቶችን አድርሷል።
በዚህም በርካታ የጋይንት እና አካባቢው ነዋሪዎች በጀግንነት ተሰውተዋል ነው ያሉት።
የህዝቡ ደጀንነት ለሰራዊቱ ትልቅ ነበር ያሉት ኮሎኔል ሽጉጤ፥ ትግሉ አሁንም አላበቃም ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ የመከላከያ ሰራዊት በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በስነስርዓቱ በውጭ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ነዋሪዎች የሃይማኖት አባቶች ጨምሮ የተጎጂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.