የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገሪቱ በተከሰተው ችግር የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚዉል አስቸኳይ የድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩን አስታወቀ።
አሸባሪው ትህነግ ባካሄደው ወረራና በፈጸመው ጥፋት ምክንያት የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን ቀውስ ተከትሎ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚዉል አስቸኳይ የድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በሰጠው በመግለጫ አስታውቋል።
ለዘመቻው ስኬትም የሃይማኖት ተቋማት “ሰብዓዊ ድጋፍ” በሚል አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100043059125 አካውንት ቁጥር መከፈቱ ተጠቅሷል።
በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Ministry of Peace Ethiopian religious institution relief fund” 010001300080 በሚል አንድ ህዝብ ለአንድ አላማ በሚል መርህ የድጋፍ ገንዘቡ እንደሚሰበሰብ ተገልጿል።
በተቀመጠው አካውንት ሁሉም ዜጋ እንዲሳተፍ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቅረበዋል።
የሚሰበሰበው ገንዘብ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚገባቸው ወገኖች በአፋጣኝ እንዲደርስም ጠይቀዋል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!