ድንቅ ዝግጅት በማሳካት የተሳተፉትን ሁሉ አመሰግናለሁ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ለተካሄደው በዓለ ሲመት ዝግጅት መሳካት ተሳትፎ ላደረጉ ምስጋና አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በእንግድነት በመሳተፍ ልዩ ክብራቸውን ላሳዩን ፣ በመልዕክቶቻቸው ልዩ ምኞታቸውን ለገለፁልን አለምአቀፍ ወዳጆቻችን እና አፍሪካዊ ወንድሞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
ተስፋችንን አጎልብተን፣ ሥጋቶችን ቀርፈን፣ እድሎችን አሟጠን፣ ፈታኞቻችንን አሸንፈን ሀገራችንን በብልፅግና ጎዳና የምናስኬድበት ዘመን ይሆናል ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል።
አባቶቻችን ሳያስደፍሯት እንዳስረከቡን እኛም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኮርቶ የሚኖርባት የአፍሪካ የነፃነት ቀንዲል ሀገርን ለልጆቻችን እናስረክባለን ነው ያሉት፡፡
መላው የሀገሬ ኢትዮጵያ ልጆች ስለሁሉም አመሰግናለሁም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን