Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ ገቢዎች ኮሚሽን ልኡካን ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ህዳር 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ  ገቢዎች ሚኒስቴር ከታንዛኒያ የገቢዎች ባለስልጣን ልኡካን ቡድንን ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከዚህ ቀደም በአቅም ግንባታና በተጨማሪ እሴት ታክስ አስተዳደርና ሌሎች ጉዳዮች የልምድ ልውውጥ ሲያደርጉ መቆየታቸውን በገቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ አቶ ነብዩ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ጎረቤት ሃገራት የሚያደርጉት የጋራ የልምድ ልውውጥ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣትም ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሃገሪቱን ገቢ በአስተማማኝ መልኩ ለመገንባት በዘርፉ የተሻለ ልምድ ካላት ኢትዮጵያ ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተመራጭ ማድረጋቸውን በታንዛኒያ ገቢዎች ባለስልጣን የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር ሚስተር ሚካኤል ጆን ተናግረዋል፡፡

ልዑካኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከልን፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትንና የጉምሩክ ኮሚሽንን ተዘዋዋረዉ መጎብኘታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.