አሸባሪውን ቡድን መደገፍ ወንጀልና ወንጀለኛን ማበረታታት ነው – ዶ/ር ጀማል ገምታ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ምዕራባውያን አሸባሪውን ህወሓት ሲደግፉ ወንጀልና ወንጀለኛን ማበረታታት መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል ሲሉ ኑሯቸውን በእንግሊዝ ሀገር ያደረጉ ምሁር ገለጹ።
ሃገራቱ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በውል ሳይገነዘቡ ሀገር ለማፍረስ ቀን ከሌሊት ከሚተጋው አሸባሪ ህወሓት ጎን ተሰልፈዋል የሚሉት ኑሯቸውን እንግሊዝ ሀገር ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛና የህክምና ባለሙያው ዶክተር ጀማል ገምታ ናቸው።
ይህን ማድረጋቸው ወንጀልና ወንጀለኛን ማበረታታት እንደሆነና ይሄም ምንም አይነት ፋይዳ እንደሌለው የሚያነሱት ምሁሩ÷ በቀድሞ የወያኔ አገዛዝ በሁርሶ ማጎሪያ ኦነግ ተብለው ለሰባት ዓመታት እንደታሰሩና ከሀገራቸው በግፍ መገፋታቸውን ይናገራሉ።
ወያኔ ዓለም ያወቀው ወንጀለኛ መሆኑን በራሴ በእስር ቤት በግፍ አጉሮ ያደረሰብኝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አንዱ ህያው ምስክር ነው ይላሉ።
ሰላምና ኢ-ፍትሃዊነት ልክ “እንደ ቀንና ሌሊት ነው” የሚሉት ዶክተር ጀማል ከህወሓት ጋር መኖር ከወንጀለኛ ጋር መኖር ነውና ይህ እንደምን ይቻላል? ሲሉ ደግመው ይጠይቃሉ።
እናም አንዳንድ ምዕራባውያን ወንጀለኛን መደገፋቸውና ማበረታታቸው ወንጀሉን መደገፋቸውንና ከኢ-ፍትሃዊነት መወገናቸውን ያሳያል ማለታቸውን ኦቢኤንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጋር ቆመናል የሚሉት እንደ አሸባሪ ሸኔ ያሉ ተላላኪዎቹ ለግል ጥቅምና ለተላላኪነት ባህላቸው እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ አስበው እንዳልሆነ ተናግረዋል።
ስለሆነም ወንጀለኛን የሚገባውን ቅጣት በመስጠት የሀገርን ሉዓላዊነት ማስቀጠል የሁሉም ሰላም ወዳድ ዜጋ ግዴታ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!